እነሆ እኛ ከእናት ሃገራችን ርቀን በታይዋን መዲና፤ታይፔ ከተማ የምንኖር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ቀን ተቆጥሮ ጊዜ አልፎ የመጣንለትን ዓላማ ከግብ አድርስን ወደ ሀገራች እስክንመለስ እግዚአብሔርን የምናመስግንበት ስለ ሐይማኖታችን የምንወያይበት መድረክ ይሆነን ዘንድ ይህን ጽዋ መርሓ ግብር በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም ጥቅምት ፪፩፤፪፻፫ ዓ ም በታይዋን መዲና ታይፔ ፤ በታይዋን ብሔራዊ ሳይንስና ስነ መላ (ቴክኖሎጂ)ዩኒቨርሲቲ ቅጽር ግቢ ውስጥ ተመሰረተ።‹ተሰመይኪ ፍቅርተ ኦ ቡርክት እምአንስት አንቲ ውእቱ ዳግሚት ቀመር እንተ ትሰመይ ቅድስተ ቅዱሳን፡- ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ የተባረክሽ ሆይ የተወደድሽ ተባልሽ ከተለዩ የተለየሽ» የእሑድ ውዳሴ ማርያም አንቀጽ ፩ ፡፡
ስለ ጽዋ ማኅበሩ
Subscribe to:
Posts (Atom)