May 11, 2011

ሙሴ ጸሊም ኢትዮጵያዊ

ሙሴ ጸሊም ኢትዮጵያዊእናትና አባቱ ፀሓይ ያመልኩ ነበረ:: ኃጥያት በሠራ ጊዜ "ተው አምላካችን ፀሓይ ይጣላሃል " ይሉት ነበረ::"ፀሓይማ አምላክ ቢሆን እስከዛሬ ባቃጠለኝ " ይላቸው ነበር:: አንድ ቀን እውነተኛውን የፀሓይ አምላክ ማወቅ ብችል ብሎ ተመኘ:: መንፈስ ቅዱስ አነሳስቶት ወደ ገዳመ አስቄጥስ (ግብጽ )ገባ:: በገዳመ አስቄጥስ የነበረ አንድ ካህን አይቶት "ሊፈጀን የመጣ ነው " ብሎ አሰበ:: እርሱ ግን ሄዶ "አምላክ ማነው አስተምረኝ " አለው:: ካህኑም ከመምህር ኤስድሮስ አገናኘው:: አስተማረው አጠመቀው ማዕረገ ምንኩስናንም ሰጠው::

40 ዘመን ከሰው ተለይቶ በዓት ዘግቶ በጸሎት ኖረ:: በኍዋላም  500 መነኮሳት ላይ ተሾመ ቀን ቀን ሲያስተምር ይውላል:: ለሊት ለሊት በረሃ ወርዶ እንጨት ሰብሮ ውኃ ቀድቶ በየደጃፋቸውላይ አኑሮላቸው ያድራል:: እነርሱ ግን ማን እንደሚያመጣላቸው አያውቁም ነበር:: አንድ ቀን ሰይጣን ይህን መልካም አገልግሎቱን ለማስተው እንጨት ሰብሮ ውኃ ቀድቶ ሲመጣ እግሩን በድንጋይ መትቶታል:: ሙሴ ግን የሰይጣን ጸብ መሆኑ ስለገባው ይበልጥ በአገልግሎቱ ጸና እንጂ አልተንበረከከም:: 
በአል በሚያደርጉበት ጊዜ "አባታችን ማዕረገ ምንኩስና ተቀብለህ ናዝዘንብለው ወደ ሊቀጳጳስ ይዘውት  ሊቀጳጳሱ ግን ባየው ጊዜ "እንዲህ ያለውን ጠቋራ ታመጡብኛላችሁን ?" ብሎ ናቀው:: ሙሴም "ገጽህ የከፋደግ አደረጉብህ " እያለ ራሱን እየገሰፀ ወጣ:: እመቤታችንም ተገልጻ  ሊቀጳጳሱን  ስጻውልቡ ንጹሕ አይደለምን ?አለችው::  ሊቀጳጳሱም ተጸጽቶ አስጠርቶ ሾመው::
ከዚህ በኋላ ከደቀመዛሙርቱ 7ቱን አስከትሎ ወደ አባ መቃርስ ሄዶ ሳለ በርበር (ሽፍቶች ) ገዳሙን ሊያቃጥሉ እነርሱንም ሊገድሉ መጡ:: እሱም ለደቀመዛሙርቱ "ከእናንተ የፈራ ይሽሽ "አለ:: "አባታችን አንተስ አትሸሽምን? አሉት :: እርሱ ግን "ሰማዕትነትን ጠልቼ እሸሻለሁን ?አለ ::      ደግሞም በወጣትነቱ የሌላ ሰው ደም አፍስሶ ነበርና እንደንስሓ እንዲሆነው ሰማዕትነትን ፊት ለፊትተጋፈጠ  በዚያም አንገቱን ሰጠ :: እርሱን ባዩ ጊዜ 6 ደቀመዛሙርት አንገታቸውን ለሰይፍ እየሰጡ ዐርፈዋል :: ሰባተኛው መነኮስ ግን ፈርቶ ጢሻ ውስጥ ተደብቆ ነበር:: ሙሴና 6 መነኮሳት ከተሰየፉ በኋላ መልአከ እግዚአብሔር 8 አክሊላትን ይዞ ወርዶ 7ቱን ለነርሱ አቀዳጅቶ አንዱ በእጁ ሲቀር አየው:: ከተደበቀበት ወጥቶ አንገቱን በመስጠት የርሱ ድርሻ የሆነችውን አክሊል ሳታመልጠው አግኝቷታል:: 
ግብጾች በሙሴ ጸሊም ስም ቤተክርስቲያን አንጸው ገድሉን አጽፈው እስከዛሬ ይዘክሩታል ያስታውሱታል::     በቅርቡም ታሪኩን የሚያሳይ ፊልም ሠርተው ለእይታ አብቅተዋል::  
በረከቱ ረድኤቱ በእኛ ላይ ይደር ! 
የሃይማኖት አጋሮቻችንን ከዘረኝነት መንፈስ ውጪ የምናይበትን የሙሴ ጸሊምንና የግብጻውያኑ መነኮሳትን ዓይነት ልቦና እግዚአብሔር ያድለን ! አሜን !

0 comments:

Post a Comment

አስተያየት ወይም መልዕክት ካልዎት፤ ከዚህ በታች ያለውን ሰሌዳ ይጠቀሙ።