2 የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት
ብሉይ ኪዳን ማለት የቆየ፣ የጥንት ውል ወይም ስምምነት ማለት ነው፡፡ ከክርስቶስ ልደት በፊት ያለውን የአንድ አምላክ አማኞች የሆኑትን የዕብራውያንን ታሪክ ይተርዳል፡፡ በውስጡም ብዙ የተስፋ ቃሎችን የያዘ ነው፡፡ ስለ መሲሕ ክርስቶስ መምጣትም የተነገሩ ትንቢቶች በብዛት አሉበት፡፡ ኢሳ 7÷14
ብሉይ ኪዳን ከሐዲስ ኪዳን ተነጥሎ አይታይም፡፡ ምክንያቱም ብሉይ ኪዳን የሐዲስ ኪዳን ትንቢት ሲሆን ሐዲስ ኪዳን የብሉይ ኪዳን ፍጻሜ ነው፡፡ ሐዲስ ኪዳን በብሉይ ኪዳን ውስጥ አለ፡፡ ሆኖም ግን ነቢያት የተነበዩለት አምላክ ወልደ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘመኑንና ጊዜውን ቆጥሮ በተገለጠ ጊዜ ስውር የነበረው ሐዲስ ኪዳን ተገልጸል፡፡ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ከተጻፋት ጊዜ ፣ ከያዙት ሀሳብና ከአጻጻፋቸው ሁኔታ አንጻር በዐራት ምድቦች ይከፈላሉ፡፡ እነርሱም፡-
2.1 የሕግ መጻሕፍት
የሕግ መጻሕፍት የሚባሉት መጽሐፍ ኦሪትም በመባል ይታወቃል፡፡ ኦሪት ቃሉ የሱርስት ሲሆን ሕግ ማለት ነው፡፡ የሕግ መጻሕፍት በቁጥር አምስት ሲሆኑ የእነዚህ መጻሕፍት ጸሐፊም ሊቀ ነቢያት ሙሴ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት አምስቱ የሙሴ መጻሕፍትም ይበላሉ፡፡ እነዚህ መጻሕፍት እንደየይዞታቸው የተለያ ስያሜ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ስያሜዎቻቸውና የየመጻሕፍቱ ይዘት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
1. ኦሪት ዘፍጥረት /ዘልደት/
ይህ መጽሐፍ የሥነ-ፍጥረትን ልደት፣ አጀማመርና አመጣጥ የሚያስረዳ በመሆኑ ይህን ስያሜ አግኝቷል፡፡ ከሕግ መጻሕፍትም ሲጻፍ የመጀመሪያው ነው፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 50 ምእራፎች ያሉት ሲሆን የመጽሐፉም ይዘት እንደሚከተለው በአራት ዋና ዋና ክፍሎች በመክፈል ሙሉ ታሪኩንና ትምህርቱን ማጥናት ይቻላል፡፡ እነዚህም ክፍሎች የሚከተሉት ናቸው፡፡
2. ኦሪት ዘጸአት
3. ኦሪት ዘሌዋውያን
4. ኦሪት ዘኁልቁ
5. ኦሪት ዘዳግም
ምንጭ
የመጽሐፍ ቅድስ ጥናት (ቁጥር 1) በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን በ/ሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማሕበረ ቅዱሳን ፤ በመ/ር አባይነህ ቸሬ አበበ እና በዲ/ን ቴዎድሮስ በየነ
የመጽሐፍ ቅድስ ጥናት ጥራዝ በመናገሻ ገ/ድ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ሰ/ት/ቤት
0 comments:
Post a Comment
አስተያየት ወይም መልዕክት ካልዎት፤ ከዚህ በታች ያለውን ሰሌዳ ይጠቀሙ።