Dec 12, 2011

የያሬድ ቤት: “መኑ ይመስለከ”/መዝ ፹፰-፮/

የያሬድ ቤት: “መኑ ይመስለከ”/መዝ ፹፰-፮/: “ዕፍረት ምዑዝ  ኢየሱስ ክርስቶስ፤ኢየሱስ ክርስቶስ መአዛዉ ያማረ ሽቶ ነዉ/ኤፌ -/አንድም ኢየሱስ ክርስቶስ ምዑዘ ባህሪይ ነዉ።ንዑ ንስግድ ሎቱ፤እንሰግድለት ዘንድ”/ፊል -/ “ወንዕቀብ ትዕዛዛቲሁ፤ትዕዛዙን እንጠብቅ ዘንድ ከመ ይሥረይ ለነ ኃጣዉኢነ፤ኃጢአታችንን ያስተሰረይልን ዘንድ /መጽሐፈ ቅዳሴ ንባቡና ትርጓሜዉ ገጽ ፹፪//ሉቃ -፳፬/።ክፉ መአዛችንን በበጎ መአዛህ የለወጥህ። በመልዕልተ መስቀል ተሰቅለህ በወርቀ ደምህ ፈሳሽነት ወደ ገነት መንግሥተ ሰማያት ያቀረብኸን መድኅነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ነህ።ውሉደ አዳም ደቂቀ አዳም የወደቀበትን የሞት የኃጢአት ዕዳ ከላዩ ለማንሳት አቅም አልነበረውም።የሰዉ ልጅ ሞቱን በሕይወት ለመለወጥ ችሎታ አልነበረውም።በባሕሪህ ምዑዝ የሆንህ አምላክ ወልደ አምላክ አንተ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ሁሉን ማድረግ ተችላለህ።ስለዚህም በሥልጣንህ ለአዳም ዘር የሚበጀውን ሁሉ አደረግህ።

0 comments:

Post a Comment

አስተያየት ወይም መልዕክት ካልዎት፤ ከዚህ በታች ያለውን ሰሌዳ ይጠቀሙ።