Mar 22, 2014

ደብረዘይት ዘሰንበተ ክርስቲያን

ምንጭ፦መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መጋቢት 12 ቀን፣ 2006 ዓ.ም.)

 እኛ ክርስቲያን እንባል ዘንድ፣ ከክርስቲያኖችም ጋር እንኖር ዘንድ፣ በዘመናችንም ሁሉ እንደኖሩት ሐዋርያት ትምህርት እንኖር ዘንድ፣ እንደ አባቶቻችን ሐዋርያት ክርስቲያን ሆነን በመቃብር ውስጥ ባንቀላፋንምበዚያ በደብረዘይት በምንነሳም ጊዜ ከእነርሱ ጋር በእነርሱ እቅፍ እንቀመጥ ዘንድ በአንተ ፍቅር ልንኖር ግድ ይለናል:: በማይለወጥ ፍቅሩ ሰላም ለእናንተ ይሁን:: “የወጉትም ያዩታል” እንዲል መጽሐፍ ዛሬ አክብረነው የምንውለው በዓል ደብረዘይት ይባላል:: ጌታችን የዚህችን ዓለም ፍጻሜ ዘመን ያስተማረባት ተራራ ነች:: በዛሬዋ ሰንበትም ሁሉን እንደ ስራውሊከፍለው የሚመጣው ተቆጣጣሪ የሥራውን ሁሉ የክፍያ መጠን ዛሬ አስታውቋል:: ሊቁ ቅዱስ ያሬድም በጾሙ ወቅት እንዳየነው ሰው የመጀመሪያ ፍጻሜውን የሥጋውን ሞት እንዲያስብ በዜማይነግረን ነበር:: ከቀናት ሁሉ የምትጨንቀውን አስፈሪዋን ደግሞ ዛሬ በማሰብ እንድንውል እጁን ወደ ላይ ልቡን ወደ አርያም አድርጎ አብረነው እንድናዜም ያዘናል:: የዚህ ሳምንት ድርሰቱ ደብረዘይትን አስቀድሞ እንዲህ ብሎ ስለሚጀምር የደብረዘይት ሳምንት ተብሏል::

“እንዘ ይነብር እግዚእነ ውስተ ደብረዘይት ወይቤሎሙ ለአርዳኢሁ ዑቁኬ ኢያስሕቱክሙ ወንበሩድልዋኒክሙ፣ በሰንበት ኢይኩን ጉያክሙ… ጌታችን በደብረዘይት ተቀምጦ ሳለ ደቀ መዛሙርቱን እንዳያስቷችሁ ተጠንቀቁ፤ ሽሽታችሁ በሰንበት አይሁን አላቸው፡፡… ካዕበ ይቤሎሙ… ዳግመኛም ኢየሱስደቀ መዛሙርቱን የመከሩ ጊዜ እንደደረሰ ምሳሌውን ከበለስ እወቁ አላቸው::” አሁን የእግዚአብሔር መንግስት በመካከላችሁ ናት:: በሕይወት የማታውቁትን እግዚአብሔርን ተሰብካችኋል፤ ተጽፎላችኋል፤ተዘምሮላችኋል:: ነገር ግን አብልጬ ስነግራችሁ አብልጣችሁ ራቃችሁኝ፡፡ ዛሬ የመጨረሻው ቀን ከበር ላይ ነው:: ሁሉ በስሜ መጥተዋል፤ በስሜ አጋንንት አወጡ፤ ወገንና ደጋፊ አበጁ፤ ግንአላውቃቸውም፤ ከእኔ አይደሉም:: በሚታረፍባት ቀን ስደት እንዳይሆንባችሁ ለጉዞ የሚሆናችሁን ስንቅ አስቀድማችሁ ያዙ:: “ አሜሃ ይበክዩ ኵሎሙ ኃጥአነ ምድር ሶበ ይሬእይዎ… የሰውን ልጅ በሰማይ ደመና በኃይል ሆኖ ባዩት ጊዜ የምድር ኃጢአተኞች ያን ጊዜ ያለቅሳሉ::” የሰው ልጅ ዛሬ በእኛ መካከል በቸርነቱ ታውቋል፤በአቅማችን ተገልጧል:: ይህን ጊዜ ምሕረቱን እያሰብን ስለ ኃጢአታችን አልቅሰን ኃጢአተኛ ከመባል እንውጣ እንጂ ያን ጊዜ በኃይል በግርማ ሲመጣ ስለ ኃጢአታችን ሳይሆን የኃጢአተኝነታችን ነገር፣ጉዳችን ግልጥ በሚሆን ጊዜ የማይጠቅመውን ልቅሶ አናልቅስ::

“አመ ይመጽዕ ወልድ በስብሐት ይትከወስ ኵሉ ኃየለ ሰማያት… ወልድ በምሥጋና በሚመጣበት ጊዜ የሰማይና የምድር ኃይል ሁሉ ይናወጣል…” ወዮ ያን ጊዜ ማን ይቆማል? ቅዱስ ያሬድ ያዜማል! ስለዚያች ቀን በሚያሳዝን ዜማው ልባችንን እየነካ ያች ቀን እየታየችው ይናገራል:: “ከመ እንተ መብረቅ ዘይወጽዕ እምጽባሕ… መብረቅ ከምስራቅ ወጥቶ እስከ ፀሐይ መግቢያብልጭ ብሎ እንደሚታይ ከሰማይ ኃይል ጋር ከመብረቆች ብልጭታ ከአእላፍ መላእክት ጋር የሰው ልጅ አመጣጡ እንዲሁ ነው:: የአክሊሎች አክሊል በካሕናት ራስ ነው::” ከቃሉ ትዕዛዝ መላእክትመለከትን ይነፋሉ:: ያን ጊዜ የትዕግስታችን ልክ ርዝመቱ ይታወቃል፤ ያን ጊዜ የሰው ንጽሕና ስፋቱ ይለካል፤ ያን ጊዜ ካሕን ወይ ሌላ፣ ያን ጊዜ ባዕለ ጸጋ ድሃ የለም፤ የሁሉም ስራው ይሰፈራል:: “አመ ዕለተ ፍዳ አመ ዕለተ እግዚአብሔር ምንተ ንብላ ለነፍስ አመ ኢታድኅን እም ውሉዳ… በመከራና በፍዳ ቀን ነፍስን ምን እንላታለን? እናት ልጇን ማዳን በማትችልበት ጊዜ፣ ምድርም አደራዋንበምትመልስበት ጊዜ፣ አባት የበደል ዋጋ ልብስን በለበሰ የበቀልን ግምጃ በለበሰ ጊዜ፣ በምታስፈራ አደባባይ በወቀሰን ጊዜ፣ ያን ጊዜ ሥራችን ሁሉ ይገለጣል፤ የሰራነው ሁሉ ይነበባል:: ጌታችንበደብረዘይት ተቀምጦ ሳለ ደቀመዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀረቡ፤ ለሰው ችግረኛን ቢያስብ በጎ ነገርን ቢሰራ በተሻለው ነበር::” መብራቱ ሳይጠፋ ዘይትን ማዘጋጀት ይበጃል::

“አመ ይመጽዕ ንጉሥ በንጥረ መባርቅት… ንጉሥ በንጥረ መባርቅት በሚመጣበት ጊዜ የዕለታት አውራ ሰንበት ትገዛለች:: ያን ጊዜ ጨረቃ፣ ፀሐይ፣ ክረምትና በጋ የለም:: የሰው ልጅ በሚመጣበት ጊዜየሰማይና የምድር ኃይል ይናወጣል፤ ኃጥአን በሕይወት ዘመናቸው ያላሰቡትን ያለቅሳሉ፤ የእሳት ጎርፍ በፊቱ ይፈሳል፤ የእሳት ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ እንደ ክረምት ውሀ እንባ ይፈሳል፤ ኃጥአን ከጻድቃንመካከል ይለያሉ ሕይወትን የፈጠረ ነውና:: ሰነበትን ለእረፍት ሰራ::” ሽባን የሚያድኑ፣ አንካሳን የሚያቀኑ፣ እውርን የሚያበሩ፣ ዓለምን የፈጠረበት ቃሉ የምህረት ምንጭ ነው:: በዚያን ጊዜ ግን ለኃጥአንከሰይፍ የከፋ ይሆናል:: ከእኔ ሂዱ ይላቸዋልና:: ከእርሱ የሄደ ምንድነው? ምንስ አለው? ስለዚህ “ስምዑ ቃልየ… ቃሌን ስሙ ህጌንም ጠብቁ::…” ይለናል:: “ንጉሥ ሁሉን ጠራ” ይላል ዜመኛው፤ “ንጉሥሁሉን ጠራ፤ የመረጣቸውን ግን በመለከት ድምጽ ሰበሰባቸው:: የእርሱን ትንሣኤ ወራሾች ኑ የአባቴ ቡሩካን ይላቸዋል::” አቤቱ እኛን ባሪያዎችህን ታድነን ትምረንም ዘንድ የሕያዋን ጌታ ማረን:: “ፀሐይ ሠረቀ ቀርን ፀርሐ… ፀሐይ ወጣ፤ ነጋሪት ተመታ፡፡ ዓዋጅ ነጋሪ ደረሰ፡፡ እውነተኛ ፍርድን ለመፍረድ ትጉሃን ይሮጣሉ፤ የደከሙ ይደሰታሉ፤ ሰነፎች ይደነግጣሉ፤ በቀኙ ያሉ የተገዙለትበሕይወታቸው የተገዙለት ፊቱን ባዩ ጊዜ ይደሰታሉ።

 እስራኤል ሕዝብህን አቤቱ አስበን:: “መሐረነ እግዚኦ ወተሠሃለነ… አቤቱ ማረን ይቅር በለን፡፡ ከእኛ ምሕረትህን አታርቅ፡፡ አቤቱ ሰላምን ምሕረትን ስጠን::” አሜን!

0 comments:

Post a Comment

አስተያየት ወይም መልዕክት ካልዎት፤ ከዚህ በታች ያለውን ሰሌዳ ይጠቀሙ።