Apr 8, 2011

“ያን ጊዜ በዚያ ወራት ይጦማሉ ሉቃ።” ፮—፫፬፡፫፮


“ያን ጊዜ በዚያ ወራት ይጦማሉ ሉቃ።፫፬፡፫፮
እንደሚታወቀው ማንኛውም ነባራዊ ሃይማኖት በራሱ ሕግና ሥርዓት የተወሰነና የተቀረጸ የአጻጽዋም ሥርዓትና ደንብ እንዳለውየታወቀ ቢሆንም አሁን እንዳለው የታወቀ ቢሆንም አሁን  በዚህ  የወንጌል መልእክት  ለመገለጽና ለመንገር የምንፈልገው ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስለምትፈጽመው ጾም ነው፡፡ ጾም በኦርቶዶስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ትምሕርትና ሕግ መሠረት በእግዚአሔር ዘንድ ከፍተኛ ጸጋን፣ክብርንና ዋጋን የሚያሰጥ ነው፡፡ጾምን መጾም እንደሚገባ መጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ቦታ ያረጋግጠዋል፡፡የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መምህራንም መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርገው መጾም አቻምና ሔዋን በገነት ሳሉ እንደተጀመረ ያስተምራሉ፡፡እግዚአብሔር ለአዳምና ለሔዋንይህንና ይህን ብሉ ያነን ግን አትብሉብሎ ያዘዛቸው የጾምን መርህ ያመለክታል ይላሉ(ዘፍ።፪፤፩፮፩፰)፡፡
ጾምን በመጾም ሰማያዊ ክብርና ፀጋ እንደሚገኝ ብዙ የሚያከራክር ባይሆንም የዘመኑ ተከራካሪዎችበሕግ የተወሰነ በጊዜም የተቆረጠ የጾም ጊዜ የለም’’ በማለት ይከራከራሉ፤ደግሞም ኢየሱስ ክርስቶስ ጾም እንድንጾም ያዘዘው ትዕዛዝ ስለሌለ ለመጾም አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ጾምን መጾም ይቻላል፤ወሩን ወስኖ መጾም ግን አስፈላጊ አይደለምእያሉም ይሟገታሉ፡፡
የጥንቱን እምነትናንና ሥረዓተ ሃይማኖትን የምትከተለው ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ግን በዘመነ ነብያት (በብሉይ ኪዳን ዘመን) ጊዜ የጾም ሰዓትና ወር በሕገ ነብያት ተወስኖ ሲሠራበት እንደነበረ ታረጋግጣለት፣ለአብነትም ያህል በነብዩ ዘካርያስ መጽሐፈ ትንቢት የአራተኛው ወር ጾም የአምስተኛው ወር ጾም።።።።።። ተብሎ የተመለከተው በዚያ ዘመንም በዕለትና ወር የተተመነ የጾም ጊዜ እንደነበረ ቤተክርስቲያን ታስገነዝባለች(ዘካርያስ፰፣፩፱)፡፡ ቅዱስ ሉቃስም በጻፈው ወንጌልም ዕቡይ (ትዕቢተኛ) ፈሪሳዊው ሲጸልይ በየሳምንቱ ሁለት ጊዜ እጾማለሁ ማለቱ በየሳምንቱ ሳይቀር በሥርዓት በተወሰነ ቀን ጾም ይጾም እንደነበረ ቤተክርስቲያን ታስረዳለች(ሉቃ።፩፰፤፱፩፫)

ስለዚህ በዚህ ነባር ሥርዓተ ሃይማኖተ መሠረት ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሰባት አጽዋማት በቀኖና ማለት በሕገ ቤተክርስቲያን በተወሰነላቸው መሠረት እንዲጾሙ ወስናለች ፡፡ ከዚህም ሌላ ተከራካሪዎቹ እንደሚሉት ሳይሆን ደቀመዛሙርቱ እንዲጾሙ ማዘዙን ከቅዱስ ወንጌል መረዳት ይቻላል፡፡
ከዕለታት ባንዱ ቀን የዩሐንስ መጥምቅ ደቀመዛሙርት ብዙ ጊዜ እንደሚጾሙ በመጥቀስ ፈሪሳውያንና ጻፎቻቸው ወደ ጌታ ቀርበው የዩሐንስ ደቀመዛሙርት ስለምን ብዙ ይጾማሉ ጸሎትንም ስለምን ያደርጋሉ፤ደግሞም የፈሪሳውያን ደቀመዛሙርት ስለምን እንደዚሁ ያደርጋሉ፤ያንተ ደቀመዛሙርት ግን ይበላሉ ይጠጣሉም አሉት፡፡ኢየሱስም ሙሽራው ከእነሱ ጋራ ሳለ ሚዜዎችን ልታስጾሙ ትችላላችሁን  ነገር ግን ወራት ይመጣል ሙሽራው ከነሱ ሲወሰድ ያን ጊዜ በዚያ ወራት ይጾማሉÈ አላቸው(ሉቃ።፭፤፫፫፡፫፮)       
ቅዱስ ማቴዎስ በጻፈው ወንጌል ደግሞ እንዲህ ተብራርቷል፤Çሙሽራው ከእነርሱ (ከሚዜዎቹ) የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል በዚያን ጊዜም ይጦማሉ በማለት እንዳስረዳቸው እንገነዘባለን(ማቴ።፱፤፩፭)፡፡ ስለዚህ በሕገ ቤተክርስቲያን የተወሰኑትን ጾም የምንጾመው በዚህ ትዕዛዝ መሠረት ነው፡፡እንድንጾም መታዘዙ ግን ጸጋንና  ክብርን ለመቀበል ነው፡፡ይልቁንም በጾምና በጸሎት ተወስኖ እግዚአብሔርን በመለመን ይቅርታና ምሕረትን ከእግዚአብሔር ማግኘት እንሚቻል መጽሐፍ ቅዱስ በብዙው ክፍል በግልጽ ያስረዳል፡፡ይህንንም ለአብነት ያህል ከዚህ በታች እንመለከታለን፡፡

ነቢዩ ሙሴ በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ወደ ሲና ተራራ ወጥቶ በዚያ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከጾመ በኋላ እግዚአብሔር ተገለጠለት፣ ከዚህም ተራራ ከእግዚአብሔር አሥርቱ ቃላት(አስሩ ትዕዛዛት)የተጻፈባቸውን ሁለት የቃል ኪዳን ጽላት ይዞ ተመለሰ(ዘፀ።፫፬፤፪፰፡፴)፡፡
ነቢዩ ሳሙኤል የእስራኤል ልጆች በምጽጳ ተሰብስበው በልቅሶና በጸሎት ጹመው ዋሉ፡፡ በዚህም ምክንያት መንፈሳዊ ኃይል ተሰጥቶአቸው ጠላቶቻቸውን ድል አረጉ (፩ኛ ሳሙ።፯፣፭፡፩፩)  
ነቢዩ ኤልያስ ነብያተ (ካህናተ) ጻዖትን ስገድሎ አብርሃም የሰበካትን ሃይማኖት በንጉሡ በአክዓብ ፊት ካስከበረና እግዚአብሔርም የአማልክት አምላክ መሆኑን ለሕዝበ እስራኤል ካስረዳ በኋላ ከአክዓብና ከኤልዛቤል ፊር ሸሽቶ ወደ ምድረ ይሁዳ መጥቶ ደክሞት በአንዲት ክትክታ ዛፍ ስር አረፈ፡፡ ከዚህም እንዳለ አንቀላፋ፡፡ ወዲያውም የእግዚአብሔር መልአክ ምግብና ውሀ ይዞ ወደ ኤልያስ ቀረበና ቀስቅሶ እዲመገብ አደረገው፡፡ ኤልያስ ተመገበና ተመልሶ ተኛ፡መልአኩም እንደገና ቀሰቀሰውና እንዲመገብ ነገረው፡፡ኤልያስም ተመግቦ ለሁለተኛ ጊዜ ተመልሶ ተኛ፣መልአኩም ለሦስተኛ ጊዜ ኤልያስን ቀሰቀሰውና የምትሄድበት መንገድ ሩቅ ነውና ተነሥተህ ብላ አለው፡፡ኤልያስም ተነሥቶ በላ ጠጣም፡፡በዚያም ምግብ ኃይል ወደ ሚሄድበት ሩቅ መንገድ እስከ እግዚአብሔር ተራራ እስከ ኮሬብ ድረስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሄደ፡፡ ኤልያስ ይህን አርባ ቀን ሲጓዝ ጾሙን እየጾመ እንደሆነ ይነግረናል፡፡ ከዚያም ቀጥሎ በኮሬብ ተራራ አጠገብ ወደ ሚገኘው ወደ አንድ ዋሻ ገባ፡፡ኤልያስ በዚያ ዋሻ በጸሎት ላይ ሳለ እግዚአብሔትር ተገለጠለት፡፡ ወደ ሰማይ ከመወሰዱም በፊት በዚያ ዋሻ ሳለ ማድረግ የሚገባውን ሁሉ እንዲያደርግ እግዚአብሔር ለኤልያስ ነገረው(፩ኛመጽ።ነገሥት ፩፱፣፩፡፩፬)፡፡
እግዚአብሔት ለኤልያስ ሊገለጽለት የቻለው ኤልያስ በጾምና በጾለት ተወስኖ እግዚአብሔርን በመለመኑ ነው፡፡ነቢዩ ኤልያስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ማንኛውም ምግብ ተከልክሎ በጾምና በሡባዔ ተወስኖ ከቆየ በኋላ እግዚአብሔር ኤልያስ ወደ ነበረበት መጥቶ ተገለጠለት፡፡ ይኸውም የጾምና የሡባዔ ውጤት መሆኑ ግልጽ ነው፡፡
ንግሥት አስቴር አስቴርና ሌሎቹ እስራኤላውያን በምርኮ በባቢሎን አገር በነበሩት ወቅት የንጉሡ የአርጤክሽ ሠራዊት ሙሉ አዛዥ የነበረው የሐመዳት ልጅ ሐማ ሕዝበ አይሁድን ከሞላው የንጉሡ ግዛት ሊያጠፋቸው ተነሣ፣ከዚያም በሐሰት ንጉሡን አሳምኖ አይሁድ በሙሉ ሐፃናቱን ሽማግሌዎቹ ሳይቀሩ እንዲገደሉና እንዲደመሰሱ በየአውራጃው አዋጅ ታወጀ፣ደብዳቤም ተሠራጨ፡፡ በዚህ ጊዜ አስቴርና አጎትዋ መርዶክዮስ እጅግ ተጨነቁ ፡፡ ያን ጊዜ አስቴር መርደክዮስ ጋር በመመካከር አይሁድ ወዳሉበት ሁሉ በመርዶክዮስ እጅ እንዲህ የሚል መልዕልት ላከች ፡፡ ለእኔ ጹሙልኝ እናንተም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ጹሙ አትብሉ አትጠጡም እኔና ደንገጡሮቼ (ሴት አችከሮቼ)ደግሞ እንዲሁ እንጾማለን።።። በማለት የአስቴር ወገኖች በሙሉ በጾም በጸሎት የሦስት ቀን ሡባዔ እንዲይዙ አደረገች ፡፡ በዚህ ምክንያት የአይሁድ ጠላት ሐማ ያሳወጀው የእልቂት አዋጅ ንግሥት አስቴር ከጾመችና ከጸለየች በኋላ ወደ ንጉሥ አርጤክሽ ቤተመንግስት ገብታ የሞቱን አወጅ አስለወጠች ፣ሕዝበ አይሁድንም ከእልቂትና ከድምሳሴ አዳነች፡፡በጾም ምክናያት እግዚአብሔር ለንግሥት አስቴር በንጉሡ ፊት ሞገስን እንድታገኝና የለመነችውን ሁሉ ንጉሡ እንዲፈጽምላት አደረገ(መጽ።አስ።፫፣፯)     
የንግሥት አስቴርና የመላ ሕዝበ አይሁድ ጠላት የነበረው የሐመዳቱ ልጅ ሐማ ግን በቅናት መንፈስ ተነሣስቶ መርዶክዮስን በዕንጨት ሰቅሎ ለመግደል በተሠራው ረዥም የዕንጨት መስቀያ ራሱ እንደተሰቀለበት ንጉሥ አርጤክሽ ስላዘዘ ሐማ ተሰቅሎ ሞተ (መጽ።አስ።፯፣፩፡፲)፡፡
ነበዩ ዳንኤል ፡፡ዳንኤል እስራኤላውያን በባቢሎን አገር በምርኮና በስደት ከነበሩበት ነብያት አንዱ ነው፡፡እሱም እግዚአብሔር ሕዝቡን ይቅር እንዲል የስደቱ ዘመንም እግዚአብሔር እንዲያሳልፈው አዘውትሮ በጾም በጸሎት እግዚአብሔርን ይለምን ነበር፡፡ በዚያ ዘመን በፋርሱ ንጉሥ በቂሮስ ዘመነ መንግሥት በነገሠ በሦስተኛው ዓመት ነቢዩ ዳንኤል ስለራሱና ስለሕዝቡ ወደ እግዚአብሔር ለመለመን ሡባኤ መግባቱን እንዲህ እያለ ይተርክልናል፡፡ Çበዚያም ወራት እኔ ዳንኤል ሦስት ሳምንት ሙሉ  ሳዝን ነበርሁ፡፡ማለፊያ እንጀራም አልበላሁም ሥጋና ጠጅም በአፌ አልገባም ሦስቱም ሳምንት እስኪፈጸም ድረስ ዘይት አልተቀባሁምÈ ይላል ታሪኩ፡፡(ዳን።፲፣፪፡፬)
ዳንኤል በዚሀ ዓይነት ጾምና ሡባኤ ተወስኖ ሶስት ሳምንት ሙሉ እግዚአብሔርነ ከለመነ በኋላ ወዲያው ቀደም ሲል በራእይ ተገልጾለት የነበረው ሰማያዊው መልዕክተኛ (መልአክ) በድጋሚ ወደ ዳንኤል መጥቶ ተገለጸለት ፡፡የተገለጸለትም መልአክ ገብርኤል እንደ ሆነ ቀደም ሲል በምዕራፍ ፱፣፪፪ ስንደተጻፈው ዳንኤል እንዲህ ብሎ ነበር፡፡ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቸው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ፣በማታም መሥዋዕተ ጊዜ ዳሰሰኝ፣አስተማረኝ፤ተናገረኝም እንዲህም አለኝዳንኤል ሆይ ጥበብንና ማሰተዋልን አሰጥህ ዘንድ አሁን መጥቻለሁ ፣አንተ እጅገ የተወደድህ ነህና በልመናህ መጀመሪያ ላይ ትዕዛዝ ወጥቶአል እኔም እነግርህ ዘንድ መጥቻለሁ ሲል ነግሮት የነበረው መልአክ በሡባኤው መፈጸሚያ እንደገና ተገልጾ ።።። ዳንኤል ሆይ አትፍራ ልብህ ያስተውል ዘንድ ሰውነጥም በአምላክህ ፊት ይዋረድ ዘንድ ካደረግህበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ቃልህ(ጸሎት)ተሰምቶአል እኔም ስለ ቃልህ መጥቻለሁ ።።።ብሎ ነገረው፡፡ ከዚህም ወደፊት የሚሆነውንና የሚመጣውን ሁሉ ገለጸለት(ዳን።፲፣፩፡፩፯)፡፡
እንግዲህ ከዚህ በላይ እንዳየነው ዳንኤል ይህን የመሰለ እጅግ አስደናቂ ራእይ ሊገለጽለት የቻለው ሱባዔ ገብቶ(ይዞ)በጾምና በጸሎት ተወስኖ እግዚአብሔርን በመለመኑ ነው፡፡ እኛም የዳንኤልን ጾምና ሡባኤ እንደ ምሳሌ አድርገን በመጠቀም በልዩ ልዩ የምግብ ዓይነት ከበለጸገ ምግብ ተቆጥበን ሥጋንና ሥጋን የመሰለውን ምግበ ትተን ወይን ጠጅንና ጠጅን (አልኮልን)ከመጠጣት ተከልክለን በጾምና በሡባኤ ተወስነን ወደ አምላካችን እንጸልያለን አምላካችንም ጾማችንንና ጸሎታችንን ተቀብሎ ኃጢያታችንን ይቅር እንደሚለንና ምሕረቱንና ቸርነቱን እንደሚሰጠን ተስፋችን እውን ነው፡፡
የነነዌ ሰዎችም በዮናስ ስብከት ሦስት ቀን ሙሉ ከማንኛውም ምግብ ተከልክለው ሡባኤ ስለገቡ  ታዞባቸው ከነበረው የእግዚአብሔር ቁጣና ድምሳሴ እንደ ዳኑ መጽሐፉ በሚገባ ያሰረዳናል(ትን።ዮናስ ፫፣፩፡፲)፡፡ ሆኖም መጾም በቀኖና(በሕግ)ከተወሰኑ ምግቦችና መጠጦች ብቻ ሳይሆን ከቁጣ ፣ከሐሜት፣ከጥል፣ከቅናት ፣ከዝሙት ፣ከስካር፣ክፉ ከመናገርና ክፉ ከማሰብ ከመሰለውም ሁሉ ልንጾም ይገባናል፡፡ ካለንም በነቢዩ በኢሳያስ እንደ ተለጸው (ኢሳ።፭፰፤፩፡፩፪) ልብስና ምግብ ለሌላቸው የሚለብሱትንና የሚበሉትን መስጠት የሚገባ ነው፡ የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን፡፡ አሜን፡፡

0 comments:

Post a Comment

አስተያየት ወይም መልዕክት ካልዎት፤ ከዚህ በታች ያለውን ሰሌዳ ይጠቀሙ።