Aug 5, 2017

እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሰዎ


ምንጭ፦ አለቃ አያሌው ታምሩ ድረ ገጽ
እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሰዎ። ጾመ ፍልሰታ እንደሚታወቀው በአገራችን ዐዋቂዎች ብቻ ሳይሆኑ ሕፃናት ሳይቀሩ የሚጾሙት ጾም ነው። ጾሙም ብዙ ጸጋና በረከት የሚያሰጥ ነው።
ይህ ጾም እንዴት እንደ ተጀመረ ታሪኩን የሚገልጸውን የድምፅ ፋይል ከታች ማግኝትይችላሉ። የድምፅ ፋይሉ የተቀረጸው በ፲፱፻፺፰ ዓ፤ ም፤ ሲሆን ያስተማሩትም አለቃ አያሌው ታምሩ ናቸው።
አባታችን ለጾመ ፍልሰታ ልዩ ፍቅር የነበራቸው ሲሆን በዚህ ጾም ጊዜ ከአባቶቻቸው እንደ ወረሱት በየዕለቱ ማለዳ ውዳሴ ማርያምንና ቅዳሴ ማርያምን በአንድምታ የመተርጐም ልምድ ነበራቸው። በየዕለቱ ማታ ማታም እንደ ዘወትር ሁሉ ውዳሴ ማርያምን በዜማ ያደርሱ ነበር።
አምላካችን ጾሙን የተባረከ ያድርግልን።

0 comments:

Post a Comment

አስተያየት ወይም መልዕክት ካልዎት፤ ከዚህ በታች ያለውን ሰሌዳ ይጠቀሙ።