Sep 28, 2012

ብዙኃን ማርያም መስከረም ፳፩ (የግሸን በዓል)



መከበሩ ስለ ሁለት ነገር ነው።

ጉባኤ ኒቂያን ይመለከታል።

የመጀመሪያው ከተፍጻሜተ ሰማዕት አንዱ ከቅዱስ ጴጥሮስ ተማሪዎች አንዱ አርዮስትቤ ጥበበ ፈጠረኒ አብ ከመ እኩን መቅድመ ኩሉ ተግባሩያለውን ንባብ ይዞወልድ ፍጡር ነውብሎ ተነስቶ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ እለእስክንድሮስ አውግዞት በዚህ ምክንያት በጉባኤ እንዲነጋገሩ የሮም ንጉስ ደጉ ቆስጠንጢኖስ በኒቂያ ጉባኤ ይሁን ብሎ አዋጅ አስነግሮ የመስከረም 21 ዕለት 2340 (43) ሊቃውንት በኒቂያ ተሰብስበዋል።

መስቀልን ይመለከታል

♥†በምድር ላይ ኃጢአትን አሰረ፤ በሲዖል ሞትን አሸነፈ፣ በመስቀል ሳለ መርገምን ሻረ፣ በመቃብር ውስጥ ፈርሶ በስብሶ መቅረትን አስቀረ። (ቅዱስ አትናቴዎስ) †♥†
♥† የጌታ ግማደ መስቀል በብዙ እንግልትና መከራ በግብጻውያን ከተወሰደብን በኋላ የግብጻውያንንም ኑሮ በግዮን ውሃ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ይግዮንን ውሃ በመገደብ በኋላ ላይ ግብጻውያን አማላጅ ልከው መስቀሉን እንመልስላችኋለን ውሃውን ልቀቁልን በማለት በብዙ መከራ እንደመጣ የቤተ ክርስቱያናችን ታሪክ ይገልጻል።   በወቅቱም በሀገሪቱ ሰማይ ዝናብ ለዘር ጠል ለመከር ከመስጠት ተከልክሎ ምድርም የዘሩባትን ከማብቀል የተከሉባትን ከማጽደቅ ተከልክላ ረሃብ ሆኗልና፤ ምናልባት ጌታ ቢታረቀን ከመስቀሉ አንዱን ወገን ላኩልን ብለው ጽፈው እጅ መንሻ ጨምረው ላኩ። ይገባዋል ብለው መክረው ዘክረው የቀኝ ክንዱ ያረፈበትን፣ ስዕለ ተኮርዖውንና ቅዱስ ሉቃስ የሳላትን ስዕለ ማርያም ላኩላቸው።
ደግማዊ ዳዊትም ሊቀበሉ ስናር ድረስ ወርደው በእልልታ በሆታ ተቀብለው ሲመለሱ እሳቸው ባዝራ ጥላቸው ከመንገድ ዐርፈዋል።
♥† ከእርሳቸው በኋላ ንጉስ ዘርዓ ያዕቆብ ወዴት ባኖረው ይሻላል? እያሉ ይህን ሲያወጡ ሲያወርዱ ጌታ በታላቅ ድምጽአንብር መስቀልየ በዲበ መስቀልብሏቸው አርአያ መስቀል ናትና አዋጅ ነግረስ በዓል አድርገው መስከረም 21 ዕለት ግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም አኑረውታል።   ብዙኃን ማርያም  መባሉ ቅሉ እንዲህ ብዙኃን የተገኙበት ስለሆነ ነው።
♥† ስለዚህ መስቀል ለምዕመናን የነፃነትታቸው፣ የዕርቃቸውና የሰላማቸው ምልክት በመሆኑ ለመስቀል ልዩ ክብር ይሰጣሉ፤ ይሰግዱለታልም። ማንኛውም ተግባር፤ ጸሎትን፣ ምግብን፣ ጉዞን፣ከመጀመራችን በፊትና ከጨረሱም በኋላ በትእምርተ መስቀል ያማትባሉ፤ በፈተና፣ በሐዘን፣ ክፉ ሐሳብ በሕሊናቸው በተፈጠረ ጊዜ ሁሉ ያማትባሉ። በከበረ ደሙ መስቀልን የቀደሰ ጌታቸው በኃይለ መስቀሉ ሁሉን ሊያደርግላቸው እንደሚችል በመታመን ይህን ያደርጋሉ፡፡እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ከፈጠረበት ጥበቡ በሚበልጥ ዓለምን ሁሉ ያዳነበት ከጥበብ ሁሉ በላይ የሆነ ጥበብ ይህ ቅዱስ መስቀል ነውና!”  ለዚህ ነው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንመስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር” (መስቀል ከሁሉ ነገር በላይ ነው)” ያሉት። ይህ የመስቀሉ ነገር አምላክን ሰው የመሆንና እስከ መሪር ሞት ያደረሰውን ለሰው ልጅ ያለውን ፍቅር ከማንከር በስተቀር ሊመረመርና ድርሰ-ነገሩ ሊስተዋል የማይቻል ረቂቅ ነው። በመሆኑም ነገረ መስቀሉ ለአንዳንዶች ፈተና ለሌሎችም ስንፍን ሆኖባቸዋል። ለሚያምኑ ምዕመናን ግን ከተና እንደወርቅ ነጥረው የሚወጡበት ነው።
♥† በእውነት ጠላቶች እውነትን ለማጥፋተ ቢዘጋጁም በእርሱ ለዓለም እውነት ተሰብኳል። አይሁድ ሰዎችንና ክርስቶስን ለማራራቅ በመስቀል ቢሰቅሉትም በመስቀል ያፈሰሰው ክቡር የሚሆን ደሙ  ዓለሙን ሁሉ ወደ እርሱ አቅርቧል። የመስቀሉ በረከት በሁላችን ላይ ይደር አሜን።
የአፄ ዘርዓ ያዕቆብ መዋ. 1427-1440 .
ግሸን ማርያም ለንግስ  የሚሄዱ ምአምናንን ይዞ የነበረ መኪና:: (2000ዓም) መኪናዋ ውስጥ የነበሩት ሰዎች ሁላ ምንም ሳይሆኑ ወጥተዋል

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘበቅዱሳኒሁ ይሴባሕ  ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለም ዓለም አሜን፡፡ ወአሜን ለይኩን ለይኩን፡

0 comments:

Post a Comment

አስተያየት ወይም መልዕክት ካልዎት፤ ከዚህ በታች ያለውን ሰሌዳ ይጠቀሙ።