Nov 15, 2014

ኅዳር ስድስት


አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ኅዳር ስድስት
፩፡- በዚች ቀን ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም፥ ከአረጋዊ ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ከስደት በሚመለሱ ጊዜ ወደ ደብረ ቊስቋም ገባ፤ በመንገድ ጕዞ ካገኛቸውም ድካም አረፉ፡፡
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን፤ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷ ከእኛ ጋር ይኑር፤ ለዘላለሙ አሜን፡፡
ሰላም ለአእጋሪከ ውስተ ደብረ ቊስቋም እለ ጌሣ
ሕፃነ ማርያም ክርስቶስ አመ ጐየይከ ደወለ ንሒሳ
ወአመ በጽሐ ህየ እንዘ ይነሥእ ኃይለ አንበሳ
እንተ ሠመርከ በኅድዓት ለነፍሱ ታፍልሳ
ሰላም ሰላም ለወልደ ዮሴፍ ዮሳ፡፡
፪፡- በዚችም ቀን የሮሜ አገር ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ፊልክስ አረፈ፡፡
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን፤ እኛንም በጸሎቱ ይማረን፤ በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር፤ ለዘላለሙ አሜን፡፡
ሰላም ለፊልክስ ሊቀ ጳጳሳት ዘተኀርየ
ሶበ ፈከረ ሐዲሰ ወአጰንገለ ብሉየ
ኵነኔ ክርስቲያን ኢይርአይ በከመ ጸለየ
ወእምቅድመ ይምክር ላዕሌሁ ዲዮቅልጥያኖስ እኩየ
ሐዋዘ ሰከበ ወኖመ ጥዑየ፡፡
፫፡- በዚችም ቀን የአባ ፍሞስ፥ የለንዲዎስ፥ የይላጥስ፥ የማርትሮስ፥ የኢላስዎስ፥ የቆርናልዮስ፥ የሱኪሮስ፥ የናውኔኖስ፥ የሊባዲቆ፥ የሲላስዮስና የሰማዕት ኤስድሮስ ማኅበር የሆኑ የሁለት መቶ ሰባ ሁለት ሰማዕታት መታሰቢያቸው ነው፡፡

0 comments:

Post a Comment

አስተያየት ወይም መልዕክት ካልዎት፤ ከዚህ በታች ያለውን ሰሌዳ ይጠቀሙ።