ጽጌ መስቀል ዘጎጃም
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ ፨ የተወደዳችሁ አንባቢያን እንደ እግዚአብሄር ፍቃድ ከዛሬ ጀምሮ በተከታታይ የኢትዮጵያውያን ቅዱሳን ታሪኮችን ማቅረብ እንጀምራለን። አስተያየታችሁን እንዲሁም ሊያካፍሉን የሚሹት የኢትዮጵያውያን ቅዱሳን ታሪክ በኢሜል ኣድራሻችን ቢልኩልን ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው። የቅዱሳኑ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን።
ጽጌ መስቀል ዘጎጃም አባቱ ዘክርስቶስ : እናቱ ሥነ ድንግል : የተወለደበት ጊዜ በሰባተኛው ክፍለ ዘመን ሲሆን : በጥር 13 ቀን ተወለደ :: በዚህም ጊዜ : ከተወለደባት ቦታ እስከ አክሱም ጽዮን ድረስ : ቀስተ ደመና ተተከለ ::የተወለደባትም ቦታ : በጎጃም ክፍለ ሃገር : በቋሪት ወረዳ : በዋሸራ ገዳም ቀበሌ ነው ::
ጻድቁ ጽጌ መስቀል በገድሉና በትሩፋቱ የታወቀ ሲሆን : በመጀመርያ በስሙ የተሠራውን ገዳም ከመትከሉ በፊት : አካባቢውን ቢባርከው : ተራራው : በአንድ ጊዜ : የአበሻ ጽድ በቀለ :: ከዚህም በኋላ :በቋሪት ወረዳ : መቅደሰ ድንግል : በእንቁዕ ቅድስት ማርያም : በዚያም አቡነ ጽጌ መስቀል ገዳም ተብሎ ይጠራል :: ገዳሙ በታላቅ አጸዶች የተከበበ ነው :: የአካባቢው ገበሬ ከገዳሙ ጽድ አይነካም :: እያንዳንዱም ቅጠል ከተቆረጠ ይታመማል :: ከብቶቹም ያልቁበታል :: ልጅም ይሞትበታል ::
ይህ ጻድቅ : እንቁዕ ማርያም አጠገብ ዱር ገደል የተባለውን ተራራ ቢባርከው : ከተራራው ላይ ጸበል ፈለቀ :: ውኃውም እንደ ባሕር ተጠራቀመ :: በክረምት አይሞላም : በበጋ አይጎድልም ::ያስደንቃል :: ጻድቁ ይቀድስበት የነበረው ልብሱ : አስደናቂው መስቀሉ : ዛሬ በዋሸራ ገዳም በክብር ተቀምጦ : በገዳሙ ተአምራትን እያደረገ ይኖራል :: በዚሁ ገዳም : ታላላቅ የአብነት መምህራን ወጥተውበታል :: ጻድቁ በተወለደ በ 91 ዓመቱ ዐርፏል :: በስሙ ሁለት ቤተክርስቲያኖች ተሰርተዋል ::
የአባታችን ረድኤት በረከት አይለየን ! አሜን !
This comment has been removed by the author.
ReplyDeleteአሜን! በእውነት መልካም ጅምር ነው፣ እግዚአብሔር ያበርታህ::
ReplyDeletei am waiting to hear about other saints
ReplyDelete