አቡነ ተክለአልፋ ኢትዮጵያዊ ፦ይህ ጻድቅ የተወለደው ሸዋ ይፋት ሲሆን ተክለአልፋ ዘ ደብረድማህ ይባላል። አባቱ ካህን አሮን ይባላል። የተወለደው በታኅሳስ 8 ነው። የስሙ ትርጉም "ለዘለዓለም የሚኖር ድንቅ ሥራ " ማለትነው። ይህ ጻድቅ ከ 72 ዐበይት ቅዱሳን መሐል አንዱ ነው። የኖረበትም ዘመን በአጼ ይስኃቅ ዘመን ነው።በደብረ ድማህ አበምኔትነት ተመርጦ 6ኛ በመሆን አገልግሏል።ጻድቁ እመሙላድ የተባለችውን ዛር የሴቶች ማኅጸን የምታበላሸውን በመቋሚያቸው እንደአውሬ አባርረዋታል። እንደሰው ተልካ ሄዳ ማኅጸንታጠፋ ስለነበረ። እንደዝንብ አበረራት። ሹመትን አልፈልግም ብሎ ጸሎቱን ብቻ የያዘ በዲማ ትልቅ ክብር ያለው አባት ነው።
በ 75 ዓመቱ በታህሳስ 8 ቀን በተወለደበት ዕለት ሲሞት የራሱ መቋሚያ መሞቱን ለመነኮሳቱ ተናገረች። "አባታችን ሞተ" ብላ ነው ያበሰረችው። በመነኮሳቱ ጻድቁ በተሾመበትና 35 ዓመታት ባገለገለበት ቦታ በደብረ ድማህ ተቀብሯል። እሱ የኖረበት ቦታ ጎፍንጭ የተባለው ቦታ ነበር ።
ከአባታችን ረድኤት በረከት ይደርብን ! ጽንስ የሚያበላሹ አጋንንትን አሁንም በጸሎታቸው ኃይል ያብርሩልን ! አሜን !
0 comments:
Post a Comment
አስተያየት ወይም መልዕክት ካልዎት፤ ከዚህ በታች ያለውን ሰሌዳ ይጠቀሙ።