May 22, 2011

መጽሐፍ ቅዱስ (ክፍል ሁለት)

1.3 የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ
1.3.1 መጽሐፍ ቅዱስን ማን ጻፈው?
የመጽሐፍ ቅዱስ ባለቤቱ እግዚአብሔር ሲሆን ጸሐፊዎቹ ግን ከእርሱ የተላኩ ቅዱሳን ሰዎች ናቸው፡፡ ብዛታቸውም ከዐርባ በላይ ነው
‹‹አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክርታስ ውሰድ ለአንተም ከተናገርሁበት ቀን ከኢዮስያስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ለእስራኤልና በይሁዳ ላይ በአሕዛብ ሁሉ ላይ የተናገርሁህን ቃል ሁሉ ጻፍበት፡፡›› ኤር 36÷2
‹‹በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ፡፡›› 2 ጴጥ 1÷5-11

1.3.2  መጽሐፍ ቅዱስ መቼና የት ተጻፈ?
መጽሐፍ ቅዱስ በተለያዩ ሰዎች እንደተጻፈ ሁሉ የተጻፈበት ዘመንና ቦታም እንዲሁ የተለያየ ነው፡፡ የመጀመሪያው መጽሐፍ መጽሐፈ ሄኖክ ከተጻፈበት 1476 . ጀምሮ የመጨረሻው ዮሐንስ ራእይ እስከተጻፈበት እስከ 96 . ድረስ ብዙ ዘመናት አልፈዋል፡፡ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን ለመጻፍ 4100 ዓመት በላይ ወስዷል ማለት ነው፡፡ ከላይ እንደተገለጸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በተለያዩ ጊዜያት እንደተጻፉ ሁሉ የተጻፉባቸው ቦታዎችም እንደዚሁ የተለያዩ ናቸው፡፡ ምሳሌ
ቅዱሳት መጻሕፍት
የተጻፉባቸው ቦታዎች
የኦሪት መጻሕፍት
ሲና ምድረበዳ
መጽሐፈ ኢያሱ
ምድረ ከነዓን(በእስራኤል)
መጽሐፈ አስቴር
ፋርስ
ትንቢተ ዳንኤል
ባቢሎን
የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት: ወደ ቆላስይስ
ሮሜ
የዮሐንስ
ፍጥሞ ደሴት
1.3.3  መጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ በምን ቋንቋ ተጻፈ?
አብዛኞቹ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት የተጻፉት በእብራይስጥ ሲሆን ትንቢተ ዳንኤል የተጻፈው ግን በአረማይክ ቋንቋ ነው፡፡ የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት በዕብራስጥ ከተጻፈው ከማቴዎስ ወንጌልና በሮማይስጥ ከተጻፈው ከማርቆስ ወንጌል ውጭ የተቀሩት የተጻፉት በዘመኑ የአብዛኛው ሕዝብ መነጋገሪያ በነበረው በፅርዕ (ግሪክ) ቋንቋ ነበር፡፡
1.4  መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ኢትዮጲያ እንዴት መጣ?
ኢትዮጲያ በዓለም ላይ ከሚገኙት ብዙ ሀገሮች ተለይታ በዘመነ ብሉይ እና በዘመነ ሐዲስ ሁለቱንም ኪዳናት በመቀበል ብቸኛ ሀገር ናት፡፡ ምንም እንኳን በዘመነ ብሉይ የቃል ኪዳን ሕዝብ ተብለው የሚታወቁት እስራኤላውያን ቢሆኑም ኢትዮጵያም በወቅቱ የዚህ ቃል ኪዳን ተካፋይ ለመሆን የበቃች ሀገር ናት፡፡ ‹‹እናንተ እስራኤላውያን ለእኔ እንደ ኢትዮጵያውያን አይደላችሁምን›› አሞ 9÷7
ይቆየን፡፡

0 comments:

Post a Comment

አስተያየት ወይም መልዕክት ካልዎት፤ ከዚህ በታች ያለውን ሰሌዳ ይጠቀሙ።