Sep 10, 2017

እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ በስላም አሸጋገራችሁ


እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ በስላም አሸጋገራችሁ



ኢትዮጵያ የወራት ሁሉ መጀመሪያ መስከረም ነው፡፡ ዘመን መለወጫ መስከረም ወር የሆነበት ምክንያትብርሃናት /ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት/ የዓመት ዑደታቸውን በጳጉሜ ወር ጨርሰው በመስከረም ወር ስለሚጀምሩ ነው፡፡ዘመን መለወጫ ቅዱስ ዮሐንስ እየተባለ ይጠራል::

ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ተብሎ ከጌታችን ስብከት አስቀድሞ እንደሚመጣና ጥርጊያውን እንደሚያዘጋጅ በነቢዩ ኢሳይያስ ተነግሮለት ነበር /ኢሳ.40.3/፡፡ በዚህም መሠረት በዘመነ ብሉይ መጨረሻና በዘመነ ሐዲስ መጀመሪያ ተነስቶ «መንግሥት ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ» «እነሆ የዓለሙን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ» በማለት ስለ ጌታችን አዳኝነት መስክሯል፤ሕዝቡን ስለ ኃጢአታቸው እየገሰፁ ንስሐ እንዲገቡ አድርጓል፡፡ ጌታችንንም በዮርዳኖስ ወንዝ አጥምቋል፡፡
የቅዱስ ዮሐንስ ዕረፍት/ምትረት ርእስ/ የሚታሰበው መስከረም ሁለት ቀን ቢሆንም እንኳን ተግባሩ በዘመነ ወንጌልና በዘመነ ሐዲስ መካከል የነበረ መሸጋገሪያ በመሆኑ የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ መታሰቢያ በዓል የብሉይ ኪዳን ምሳሌ ከሚሆነው ካለፈው ዓመት የሐዲስ ኪዳን ምሳሌ ወደሚሆነው አዲሱ ዓመት መሸጋገሪያ በሆነው በመስከረም አንድ ቀን እንዲከበር፤ በዓሉም በእርሱ ስም እንዲሰየም አባቶ ወስነዋል፡፡
ቅዱስ ዳዊት በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃለህ(መዝ. 64/65:11) እንዳለ ሰዓታትን ቀናትን ወራትን ዓመታትን የፈጠረ አምላክ የሰው ልጅ መልካም ምግባራትን ይሰራባቸው ዘንድ ነው::የሰው ልጅ ክፍ የሰራባቸውን ያሳለፋቸውን ዘመን ንስሐ ገብቶ በአድስ ሕይወት ሊመላለስ ይገባዋል:: ቅዱስ ጳውሎስ ለጢሞቲዎስ  ምዕመናን በአድስ ዘመን ከክፋት ተመልሰው በጎ ስራ መስራት እንዳለባቸው እንድህ ብሎ ጽፎለታል “እውነተኛውን ሕይወት ይይዙ ዘንድ፥ ለሚመጣው ዘመን ለራሳቸው መልካም መሠረት የሚሆንላቸውን መዝገብ እየሰበሰቡ፥ መልካምን እንዲያደርጉ በበጎም ሥራ ባለ ጠጎች እንዲሆኑ፥ ሊረዱና ሊያካፍሉም የተዘጋጁ እንዲሆኑ ምከራቸው። " (1ኛ ወደ ጢሞ 6: 18-19)
የሰው ልጅ መመላለሱ በስጋ ለስጋ  ብቻ መሆን የለበትም :: በተሰጠው ዕድሜ ሰማያዊ መዝግብን ይስበስብ ዘንድ በወንጌል ተጽፏል::ቅዱሳን መላእክት ስለ ሰው ልጅ ዘመን ይለምናሉ::(ሉቃ 136-9) መልካም ፍሬ ያፈራበት ዘንድ ካለፈው ዓመት በተሻለ መልኩ ንስሐ ገብቶ በጎ ስራ ያከናውን ዘንድ የዘንድሮን ተዋት ብለው  ከአምላክ ዘንድ ዕድሜ ይለምኑለታል
ስለዚህ ዘመናችንን ለንጠቀምበት ይገባል::ቅዱስ ጴጥሮስ  “ የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና። "(1ኛ የጴጥ 4: 3) እንዳለ ከክፉ ተግባራችንን ትተን ንስሐ ገብተን በአዲስ ዓመት አድስ ህይወት ሊኖራን ይገባል::


ረድኤተ  እግዚአብሔር አይለየን









0 comments:

Post a Comment

አስተያየት ወይም መልዕክት ካልዎት፤ ከዚህ በታች ያለውን ሰሌዳ ይጠቀሙ።