መፃጉዕ (የዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት)

«ተንሥዕ ንሣዕ ዓራተከ ወሑር፤ ተነስተህ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ» /ዮሐ.5፡8/ የዐቢይ ፆም አራተኛው ሳምንት መጻጉዕ ይባላል፡፡ ይህ ዕለት አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያንን መፈወሱ የሚዘከርበት ሳምንት ነው፡፡

ዘወረደ (የዐቢይ ጾም አንደኛ ሳምንት)

ቅድስት ቤተክርስቲያናችን የዐቢይ ጾም የመጀመሪያውን እሁድ ዕለት “ዘወረደ” በማለት ትጠራዋለች። እግዚአብሔር በገባዉ ቃልኪዳን መሰረት “…የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ” እንዳለ ሐዋርያዉ ቅዱስ ጳዉሎስ የጠፋዉን አዳም ፍለጋ ከአባቱ እሪና ሳይጎድል ሳይለይ ከሰማይ መዉረዱን የምናዘክርበት በዓል ነዉ።

ጾመ ነነዌ

የነነዌ ጾም ከሰባቱ የቤተክርስቲያን አጽዋማት አንዱና የዐቢይ ጾም ማዘጋጃ ደወል ነው፡፡

ጾመ ነቢያት

“ነቢያት ሰበክዎ ሰማዕተ ኮንዎ ፈኑ እዴከ ለወላዲ ይብልዎ” (ድጓ ዘአስተምህሮ ገጽ ፻፷ /፻፷/) ነቢያት ሰበኩት፤ ምስክርም ሆኑት፤ የባህርይ አባቱን አብንም ቀኝ እጅህን ላክልን አሉት።

መስቀሉ የት ነው ያለው? ክፍል ፩

በእምነት ታሪክ ውስጥ የታሪክ፣ የአርኬዎሎጂ እና የቅርስ ጥናት ሰዎችን ያስጨነቁ ሁለት ጥያቄዎች አሉ፡፡ ታቦተ ጽዮን እና ጌታ የተሰቀለበት መስቀል የት ነው ያሉት? የሚሉት ጥያቄዎች፡፡

ጾመ ፍልሰታ

ጾመ ፍልሰታ ሐዋርያትን አብነት አድርገው ሐዋርያት የተቀበሉትን በረከት ለማግኘት ኦርቶዶክሳዊያን የሚጾሙት ጾም ነው።

«ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ ወእግዚእነ በቃለ ቀርን» /መዝ. ፹፮፥፩/

ወዘንተ እንዘ ይብሎሙ ተለዐለ ወነሥአቶ ደመና ወዐርገ ሰማየ እንዘ እሙንቱ ይኔጽሩ ኀቤሁ ወተሠወረ እምአዕይንቲሆሙ። የሐዋ.፩፥፱ ።

«መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው» /መዝ. ፹፮፥፩/

የዛሬ 2020 ዓመታት ወደኋላ ዘወር ብለን ስንመለከት ታሪክን የሚለውጥ አንድ ድንቅ ክስተት መፈጸሙን እናገኛለን።

ጌታችን እና መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፣ ሐዋርያትና ቤተ ክርስቲያን ከትንሳኤ እስከ ዕርገት

የጌታችን ትንሳኤ በአበው ዘንድ በምሳሌ የተመሰለ፣ በነቢያት በትንቢትና በምልክት የተነገረ፣ በተስፋ የተጠበቀ የድኅነታችን ታላቅ በር ነው።

ሥርዐተ ሰሙነ ሕማማት

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከዕለተ ትንሣኤ በፊት ያለውን ሳምንት ሰሙነ ሕማማት በማለት ታከብረዋለች። የዚህ ስያሜ መነሻም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መከራው፣ሕማሙና ሞቱ የሚዘከርበት ከአዳም እስከ ክርስቶስ የነበረው የዓመተ ፍዳ የዓመተ ኩነኔ ወቅትም የሚታሰብበት ስለሆነ ሰሙነ ሕማማት ተብሏል። ፡፡;

ኢትዮጵያዊው ብርሃን

ለጽንሰትከ፡-ተክለ ሃይማኖት ሆይ አስቀድሞ በማህጸን ለተጸነስከው ጽንሰትህና በታህሳስ 24 ቀን ለተወለድከው ልደትህም ሰላም እላለሁ፡፡

Sep 20, 2011

የመስቀል በዓል ክርስቲያናዊ አከባበር

/ አሉላ መብራቱ
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከምታከብራቸው ዘጠኙ የጌታችን ንዑሳን በዓላት አንዱ መስከረም 17 የሚከበረው የመስቀል በዓል ነው፡፡ መስቀል የሰላማችንና የድኅነታችን የመቀደሳችን አርማ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጆች ለማዳን፥የዘላለም ሕይወትን ለመስጠት መስዋዕትነት የከፈለበት ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ያፈሰሰበት መንበር፥ ሲሆን አምላካችንን የመንመለከትበት መስታወት ነው።
ይህ ዕለት 300 ዓመታት በላይ ጠፍቶ የነበረውን ቅዱስ መስቀል በንግሥት ዕሌኒ አማካኝነት መገኘቱን የምንዘክርበት በዚህም ደስ የምንሰኝበት ዕለት ነው፡፡ በዓሉ በምን ምክንያት እንደሚከበር ታሪኩን፣ በቅድሰት ቤተ ክርስቲያን ካህናቱና ምእመናን በአንድነት በመሆን እንዴት እንደሚያከብሩት፣ ምእመናን በየአካባቢያቸው በየቤታቸው እንዴት እንደሚያከብሩት ቀጥለን እንመልከት፡፡

መጽሐፈ ሄኖክ ( ክፍል ፪ )


ግርማዊነታቸው የተባሉ ጸሐፊ ስለ መጽሐፈ ሄኖክ ዋርካ በተስኘ ድረ ገጽ የጻፉትን በድምጽ አቀናብረን አቅርበነዋል

ክፍል ፪

Sep 11, 2011

የዘመን መለወጫ በዓል

ክቡር አለቃ አያሌው ታምሩ
ምንጭ ፦ http://www.aleqayalewtamiru.org


የዘመን መለወጫ በዓል የታወቀው ፫ ዐይነት ነው። አንደኛ እስራኤል በብሉይ ኪዳን ያከብሩት የነበረው ሚያዝያ ፩ ቀን፤ ሁለተኛ የዓለም ክርስቲያን የክርስቶስን ልደት ተቀዳሚ በማድረግ የሚያከብሩት ጥር ፩ ቀን፤ ሦስተኛ ኢትዮጵያ ጥንት መሠረቱን መሠረትነቱን ዐውቃ የምታከብረው መስከረም ፩ ቀን ነው። እስራኤል የዘመን መለወጫ በዓልን በሚያዝያ ማድረጋቸው፤ በዚሁ ወር ከግብጽ ባርነት ነጻ ስለ ወጡና እግዚአብሔር ይህንን የነጻነት በዓል በየዓመቱ እንዲያከብሩ ስላዘዛቸው መሆኑና የዓለም ክርስቲያን ጥር ፩ ቀን ማክበራቸው የክርስቶስን ልደት ምክንያት በማድረግ መሆኑ የታወቀና ብዙ ማተት የማያሻው ስለ ሆነ፤ ለወጣቶች አስቸጋሪ መስሎ ስለሚታያቸው ስለ ኢትዮጵያ ዐውደ ዓመት መስከረም ፩ ቀን ዐሳባችንን እንሰጣለን።

ኢትዮጵያ ይህንን በዓል የተቀበለችው ከካም ነው። የተጀመረበትም ካምና ኩሳ ልጁ ወደ ኢትዮጵያ የገቡበት፥ አኵስም በኩሳ ስም የተመሠረተችበት ጊዜ ነው። ዘመኑም በኢትዮጵያ ላይ ከአራት ሺሕ ዘጠኝ መቶ በላይ ሲሆን፤ ከጥፋት ውሃ በኋላ በኖኅ ዕድሜ በስድስት መቶ አንድ ዓመት ጀምሮ ሲከበር ዐምስት ሺሕ ዐምስት መቶ ዐምሳ ሁለት ዓመት አሳልፎ እነሆ ደርሰንበታል። ኖኅም ሲያከብረው ጥንቱን ዓለም የተፈጠረበት ወር እንደ መሆኑ መጠን፤ ከአዳም ጀምሮ የወረደ፥ በአበው እየተላለፈ እስከሱ የደረሰ እንደ መሆኑና ኋላም የቀላይ አፎች የተከፈቱበት፥ የጥፋት ውሃ መጕደል የጀመረበት፥ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጥፋት ውሃ ወዲህ ክረምትና በጋ መፈራረቅ የጀመሩበት፥ ምድር የፍሬ ፅንስ የአበባ መልክ ያሳየችበት ስለ ሆነ ነው።


Sep 10, 2011

ሥጋውን ደሙን እንደተቀበለ ይሆንለታል

በ ዲ/ን ኅብረት የሺጥላ
ምንጭ፦ ማኅበረ ቅዱሳን ህብር ሚዲያ መካነ ድር ( http://multimedia.eotc-mkidusan.org/video/?video=2459824646)

ቅዱስ ሩፋኤል ጦቢት እና ጦቢያ

ምንጭ፦ ዲያቆን መልአኩ እዘዘው
http://www.melakuezezew.info/
ስለዚህ እንግዶችን መቀበል አንርሳ፡፡ በዚህም ምክንያት አንዳንዶች ሳያውቁ የመላእክትን እንግድነት ተቀብለዋልና፡፡ ዕብ. 13.1-2 ፡፡
በየዓመቱ ጳጉሜ 3 የቅዱስ ሩፋኤል መልአክ መታሰቢያ ነው ፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል የጦቢትን ዓይን ያበራና ወለተ ራጉኤልን ተቆራኝቷት ከነበረው ጋኔን ያላቀቃት መሆኑ በመጽሐፈ ጦቢት በስፋት ተገልጿል፡፡
ጦቢት በፋርስ ንጉሥ በስልምናሶር ዘመን የተማረከ ከነገደ ንፍታሌም የተወለደ ጽኑዕ እሥራኤላዊ ነው፡፡ እግዚአብሔር በስልምናሶር ፊት የመወደድን ግርማና ባለሟልነትን ስለ ሰጠው አለቃ አድርጎ ሾሞት ነበር፡፡ ለወገኖቹ ምጽዋት በመስጠት ሕገ ርትዕን በመሥራት የተጋ ሰው ነበር፡፡ ሐና የምትባል ሚስት አግብቶ አንድ ልጅ ወልዷል፡፡ ስልምናሶር ሞቶ ሰናክሬም በነገሠ ጊዜ ከሹመቱ ስለሻረው ደግሞ ወደ ምድያም መሔድ አልቻለም፡፡